የሎዛ አበራ ቡድን በቻምፒየንስ ሊግ እንደሚሳተፍ ተረጋግጧል

ሎዛ አበራ የምትገኝበት የማልታው ክለብ ቢርኪርካራ በሴቶች እግርኳስ ትልቁ መድረክ ላይ መሳተፉ ተረጋግጧል።

የማልታ እግር ኳስ ፌደሬሽን በስሩ የሚያካሂዳቸው ውድድሮች መሰረዙን ተከትሎ የዓምናው የሊጉ አሸናፊ እና ውድድሩ እስከተቋረጠበት ድረስ ሊጉን ከተከታዩ ምጋር በ6 ነጥቦች በመራቅ ሲመራ የቆየው ቢርኪርካራ በቀጣይ ዓመት በቻምፒየንስ ሊግ እንዲሳተፍ የፌደሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስኗል። በመጀመርያ ዓመት የማልታ ቆይታዋ እጅግ የተሳካ ዓመት ያሳለፈችው ሎዛ አበራም ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር ያላትን ውል የምታራዝም ከሆነ በትልቁ መድረክ ላይ ትሳተፋለች።

ሎዛ አበራ የማልታ ሴቶች ሊግ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ 30 ጎሎችን በማስቆጠር የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን እየመራች እንደነበር ይታወሳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: