ሀዲያ ሆሳዕና አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ወስኗል

ነብሮቹ ከጸጋዬ ኪዳነማርያም ጋር ያላቸው ውል በመጠናቀቁ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ከውሳኔ ላይ መድረሳቸው ታውቋል።

ለቀጣይ ውድድር ዓመት አሰልጣኝ ለመቅጠር ከወዲሁ ሥራዎች በመጀመር ከፀጋዬ ኪዳነማርያም፣ አሸናፊ በቀለ እና በፕሪምየር ሊጉ ከታዩ ወጣት አሰልጣኞች አንዳቸውን ለመሾም እያጤነ የቆየው የሀዲያ ሆሳዕና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ አሸናፊ በቀለን አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ወስኗል።

የተሰረዘውን የውድድር ዓመት በአዳማ ከተማ ያሳለፉት የቀድሞው የባንኮች፣ መከላከያ፣ ሲዳማ ቡና፣ ወላይታ ድቻ እና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በቀጣይ ቀናት ከክለቡ ጋር በጥቅማ ጥቅም እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ የሚስማሙ ከሆነ በድጋሚ ወደ ደቡብ በማቅናት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ይሾማሉ።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ