ሀዲያ ሆሳዕና የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር አከናወነ

ሀዲያ ሆሳዕና አሸናፊ በቀለን በይፋ አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል።

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጋር የነበራቸውን ውል አጠናቀው አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ሆሳዕናዎች አሸናፊ በቀለን ለመሾም ከውሳኔ ላይ መድረሳቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ከአሰልጣኙ ጋር በጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ከስምምነት በመድረሳቸው በአንድ ዓመት ውል ክለቡን ለማሰልጠን የቅጥር ስምምነት አከናውነዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በተደጋጋሚ ካሰለጠኑት ባንኮች ቡድን በተጨማሪ በመከላከያ፣ ሲዳማ ቡና፣ አዳማ ከተማ የሰሩ ሲሆን ለአጭር ጊዜ የሰሩበት ወላይታ ድቻን በመልቀቅ በተሰረዘው የዘንድሮው የውድድር ዓመት አዳማ ከተማን በድጋሚ ተረክበው ሲመሩ እንደነበር ይታወሳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ