ወልቂጤ ከተማ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል

ወልቂጤ ከተማ የዋና አሰልጣኙ ደግአረግ ይግዛው ውልን ለተጨማሪ ዓመታት አራዝሟል።

በተሰረዘው የ2012 የውድድር ዓመት ላይ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ተሳታፊ መሆን የቻለው ወልቂጤን የተረከቡት የቀድሞው የአውሥኮድ እና ኢኮሥኮ አሰልጣኝ ደግአረግ ለሊጉ አዲስ እንደመሆናቸው አጀማመራቸው ደካማ የነበረ ቢሆንም ቀስ በቀስ ከሊጉ ጋር በመላመድ ቡድኑ ከፍተኛ መሻሻል እንዲያሳይ ረድተዋል። ይህን ተከትሎም የክለቡ ቦርድ የአሰልጣኙን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለማራዘም ከስምምነት ላይ ሊደርስ ችሏል።

ወልቂጤ ከተማዎች ውላቸው የተጠናቀቁትን የማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደመቀላቀሉ የፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንዲሚገቡ አያይዘው አስታውቀዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ