“ሊጉን በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ በመስከረም ወር ጨረታ እናወጣለን” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሰዮን ማኅበር ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ሊጉን በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ መታቀዱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዛሬው ዕለት የፕሪምየር ሊግ ክለቦችን በካፍ የልህቀት ማዕከል ሰብስቦ ውድድሮች የሚጀመሩበትን መንገድ በተመለከተ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ ወቅትም ሃሳቦቸን ሲሰነዝሩ የነበሩት የሊግ አክሲዮን ማኅበሩ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ሊጉን በቀጣይ በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ መታቀዱን ሲናገሩ ተሰምቷል።

“ሊጉን በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ አስበናል። በዚህም መስከረም 15 ጨረታ እናወጣለን። በጨረታውም ሃገር አቀፍ እና ዓለማቀፍ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ። እርግጥ ስለ ጉዳዩ ወደፊት በጠቅላላ ጉባዔ ዝርዝር ገለፃዎች እናቀርባለን። ግን እግረ መንገዴን ስለ ጉዳዩ ልንገራችሁ ብዬ ነው።”

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ