ዜና እረፍት | ወጣቱ ተከላካይ በድንገት ሕይወቱ አለፈ

በነቀምት ከተማ የተከላካይ ስፍራ እየተጫወተ የነበረው ቹቹ ሻውል ትናንት በድንገት ሕይወቱ አልፏል፡፡

ሀዋሳ በተለምዶ ውቅሮ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተወልዶ ኳስን በአካባቢው በሚገኝ ኮረም ሜዳ ላይ እየተጫወተ ያደገው ይህ የተከላካይ ሥፍራ ተጫዋች እግር ኳስን በክለብ ደረጃ በኢኮሥኮ፣ ቡታጅራ ከተማ እና ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በነቀምት ከተማ በጥሩ ብቃት ሲጫወት ቆይቷል፡፡ ተስፋ ተጥሎት የነበረው ይህ ተጫዋች ትናንት ጠዋት ልምምድ ሰርቶ እንደነበር የታወቀ ሲሆን አመሻሽ ላይ ከጓደኞቹ ጋር እያለ በድንገት ህይወቱ አልፏል። እስካሁንም የሕልፈቱ ምክንያት በግልፅ አልታወቀም፡፡

የተጫዋቹ አስክሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ምኒሊክ ሆስፒታል የሚያመራ ሲሆን ነገ ከሰዓት የቀብር ስነ ስርዓቱ በሀዋሳ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ በቹቹ ሻውል ሕልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለጓደኞቹ፣ ለአድናቂዎቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ትመኛለች፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!