የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ቅሬታን እያሰሙ ይገኛሉ

የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ለወራት የቆየው የደሞዝ ጥያቄያችን አልተመለሰም በማለት ቅሬታቸው እያሰሙ ይገኛል።

በርካታ ክለቦች ከወርሀዊ የደመወዝ ክፍያ ጋር በተገናኘ ጥያቄ እየተነሳባቸው ይገኛል፡፡ ከነዚህም ክለቦች መካከል በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተወዳደረ የሚገኘው ስሑል ሽረ ተጫዋቾቹ ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተገናኘ ተደጋጋሚ የይከፈለን ቅሬታን እያሰሙ ይገኛሉ። ቁጥራቸው በርከት ያሉ የክለቡ ተጫዋቾች “እስከ አሁን ምንም አይነት ደመወዝ እያገኘን አይደለም። ለክለቡን አመራሮች በተደጋጋሚ እንዲፈፀምልን ብንጠይቅም አጥጋቢ ምላሽን ማግኘት አልቻልንም። አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ጥያቅያችን ሰሚ አጥቷል።” ሲሉ ለድረ ገፃችን ቅሬታቸውን ገልፀዋል። የተጫዋቾቹ የደመወዝ ክፍያ ከአራት እስከ ስድስት ወራት ያህል ሳይከፈል መቆየቱንም አያይዘው ነግረውናል፡፡ በደሞዙ አለመከፈል ምክንያትም ችግር ውስጥ እንደሆኑ ገልፀው ክለቡ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የተጫዋቾቹን ጥያቄ ይዘን ምላሽ እንዲሰጡን የክለቡን ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋይ ዓለምን ብንጠይቅም ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ መሆን ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

በአሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃም የሚመራው ስሑል ሽረ ምንም እንኳን የ2013 የውድድር ዘመን እጣ ፈንታ ባይታወቅም እስካሁን ምንም አይነት ቅድመ ዝግጅት ካልጀመሩ ክለቦች አንዱ ነው፡፡

🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!