በቅርቡ ሕይወቱ ላለፈው ተጫዋች ቤተሰቦች የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

በነቀምት ከተማ በተከላካይ ሥፍራ ላይ ሲጫወት የነበረው እና በድንገት ከሳምንት በፊት ሕይወቱ ያለፈው ቹቹ ሻውል ቤተሰቦችን ለመደገፍ ይቻል ዘንድ የእርዳታ ጥሪ ቀረበ፡፡

የቀድሞው የቡታጅራ፣ ኢኮሥኮ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በነቀምት ከተማ እየተጫወተ የሚገኘው ቹቹ ሻውል ከሳምንት በፊት በድንገተኛ አደጋ ሕይወቱ ማለፉ ይታወቃል። የተጫዋቹ አሟሟትም በርካታ የስፖርቱ ማኅበረሰብን በእጅጉ ያሳዘነ እንደነበረም ይታወሳል፡፡ ተጫዋቹ በሕይወት በነበረበት ወቅት ቤተሰቡን የሚያስተዳድረው እሱ በመሆኑ እና አሁን ላይ በሕይወት አለመኖሩን ተከትሎ ቤተሰቦቹ ዘላቂ የሆነ መተዳደሪያ እንደዲኖራቸው በማሰብ የባንክ ደብተር በመክፈት እና ኮሚቴ በማቋቋም የተለያዩ ድጋፎች መደረግ የጀመሩ ሲሆን በቀጣይም ስፖርተኞች፣ ክለቦች እና የተለያዩ ተቋማት በወላጅ እናት እና አባቱ በተከፈተ አካውንት መለገስ እንዲችሉ ነው ጥሪ የቀረበው፡፡

የቹቹ ሻውልን ቤተሰቦች ለመደገፍ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – 1000342990561


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!