ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ ሁለተኛ ተጫዋቹን አስፈረመ

የመስመር አጥቂዋ መሳይ ተመስገን የመከላከያ ሁለተኛ ፈራሚ ሆናለች፡፡

ከቀናት በፊት አሰልጣኝ በለጠ ገብረኪዳንን የመደቡት መከላከያዎች በአሰልጣኙ ሹመት ቀን ነፃነት ፀጋዬን ከአዳማ ከተማ ማስፈረማቸው የሚታወሶ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ወጣቷ የመስመር አጥቂ መሳይ ተመስገንን በሁለት ዓመት ኮንትራት አስፈርመዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የተገኘችውና በኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለት ተስፋ ሰጪ የውድድር ዓመታት ያሳለፈችው ተጫዋቿ ከአዳማ ከተማ ጋር ቅድመ ስምምነት ብትፈፅም ለመከላከያ ለመጫወት ዛሬ በይፋ ፈርማለች፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!