ከፍተኛ ሊግ | አርባምንጭ ከተማ ስድስት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሦስት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

ከሰሞኑ የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ኮንትራት ያራዘሙት አርባምንጭ ከተማዎች ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የሦስት ነባሮችን ውል ማራዘሙን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስንታየው ንጉሴ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

አዲስ የፈረሙ ተጫዋቾች በላይ ገዛኸኝ (ከቡታጅራ ከተማ / አጥቂ)፣ አዮብ በቀታ (ከሀድያ ሆሳዕና / ተከላካይ)፣ ሙና በቀለ (ከጌዲኦ ዲላ / ተከላካይ)፣ አሸናፊ ፊዳ (ከጋሞ ጨንቻ /ተከላካይ)፣ ናትናኤል ሰለሞን (ከጌዲኦ ዲላ የመስመር አጥቂ)፣ ስንታየው አሸብር (ከሀላባ ከተማ / አጥቂ) አዳዲስ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሲሆኑ በክለቡ ውላቸው ተጠናቆ የነበሩት አጥቂው ፍቃዱ መኮንን፣ የናይጄሪያ ዜግነት ያለው ግብ ጠባቂ ጉድ ኒውስኦኮሮ እና ተከላካዩ ማርቲንስ ኦቼ ውላቸውን ለአንድ ተጨማሪ አመት ያደሱ መሆናቸውን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ያደረሰው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ክለቡ በቀጣዮቹ ቀናትም ተጨማሪ አዳዲስ ዝውውሮችን እና ውላቸው የተጠናቀቁትንም ተጫዋቾች ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም በድርድር ላይ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!