ከፍተኛ ሊግ | መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

መከላከያ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረሙ ቀጥሎ ካርሎስ ዳምጠው እና ወንዱ አብሬን አስፈርሟል፡፡

ካርሎስ ዳምጠው ከአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ጋር ዳግም በመከላከያ ተገናኝቷል፡፡ ከአርሲ ነገሌ የተገኘው እና ከዚህ ቀደም ለመከላከያ መጫወት የቻለው ሁለገቡ ካርሎስ በመቐለ 70 እንደርታ፣ ጅማ አባቡና እና ዓሞና ደግሞ እስከ ውድድር ዓመቱ አጋማሽ በወልዋሎ የተጫወተ ሲሆን በመቐለ እና ወልዋሎ ካሰለጠነው አሰልጣኝ ጋር ለሦስተኛ ጊዜ ለመሥራት ለቀድሞ ክለቡ ፊርማውን አኑሯል፡፡

ሌላኛው የመከላከያ ፈራሚ ወንዱ አብሬ ነው፡፡ የአጥቂ ሥፍራ ተጫዋቹ ዓምና በመጀመሪያው ዙር የከፍተኛ ሊግ ውድድር በኢትዮ ኤሌክትሪክ ዓመቱን ጀምሮ አጋማሽ ላይ ቡድኑን ከለቀቀ በኃላ ለለገጣፎ ለግማሽ ዓመት ቢፈርምም በኮቪድ 19 ውድድሩ በመቋረጡ እና ውል የሌለው በመሆኑ ዘንድሮ ለመከላከያ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!