ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መቐለ 70 እንደርታ አምስት ተጫዋቾችን አስፈረመ

የበርካታ ነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ የገቡት መቐለ 70 እንደርታዎች አምስት ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

ተከላካይዋ ሀና ተስፋዬ ተከላካይ ከአቃቂ ቃሊቲ፣ የመስመር ተጫዋቿ ትዕግስት ዘውዴ ከንግድ ባንክ፣ የመስመር ተጫዋቿ ቤተልሄም ከፍያለው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ አማካይዋ ቤተልሄም አሰፋ ከድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም አጥቂዋ ትንቢት ሳሙኤል ከአቃቂ ቃሊቲ አዳዲሶቹ የክለቡ ፈራሚዎች ሆነዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!