ከፍተኛ ሊግ| ገላን ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

የከፍተኛ ሊጉ የምድብ ሀ ተካፋዩ ገላን ከተማ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በማስፈረም ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡

በቅርቡ አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድን ዋና አሰልጣኝ በማድረግ የቀጠረው ገላን ከተማ በያዝነው ሳምንት ለከፍተኛ ሊጉ ውድድር ቅድመ ዝግጅቱን የጀመረ ሲሆን አዳዲስ እና ነባሮቹን አጣምሮም ልምምዱን ቀጥሏል፡፡ በሊጉ በምድብ ሀ ስር የሚገኘው ቡድኑ አስራ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን የስድስት ነባሮችንም ኮንትራት አራዝሟል፡፡

አዳዲስ ፈራሚዎች

ተከላካዮች፡- ተስፋዬ ታምራት (ከኢኮሥኮ)፣
ተመስገን ዙማ (ከኮልፌ)፣ ቻላቸው መንበሩ (ከነቀምቴ)፣ ፀጋ ዓለማየሁ (ከኢኮሥኮ)፣ ዝናቡ ባፋ (ከደቡብ ፖሊስ)

አማካዮች፡- ቢኒያም ካሳሁን (ከኢትዮጵያ ቡና)፣ ሙሉቀን አዲሱ (ከነቀምቴ) እዮብ ገብረማርያም (ከኮምቦልቻ)፣ ሳሙኤል በለጠ (ከወልዲያ)፣ አብዱለጢፍ ሙራድ (ከኢኮሥኮ)፣ መሳይ

አጥቂዎች፡- ያሬድ ታረቀኝ (ከአሶሳ)፣ ኪቲካ ጅማ (ከጅማ አባቡና)፣ ከማል አቶም (ከሻሸመኔ)

ውላቸው የተራዘመላቸው ነባር ተጫዋቾች ፡- ውብሸት ጭላሎ፣ ጅብሪል አህመድ፣ ዓለማየሁ ኃይሉ፣ ታምራት ኃይለሚካኤል፣ ያሬድ እሸቱ፣ ተሾመ መንግሥቴ


© ሶከር ኢትዮጵያ