​ወደ ካፍ ያመራው የመቐለ 70 እንደርታ ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሆነው መቐለ 70 እንደርታ ባለው የተጫዋች ብዛት ለመሳተፍ ለካፍ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ።

የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ መቐለ 70 እንድርታ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ከሊቢያው አህሊ ቤንጋዚ ጋር ግብፅ ላይ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ጨዋታ እንዲያደርግ ካፍ አስቀድሞ መርሐግብር ቢያወጣም አሁን ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ አንፃር መቐለ 70 እንደርታን በጫዋታው ላይ አስራ አንድ ተጫዋቾችን በመያዝ ወደ ግብፅ በማቅናት መካፈል እንዲችል ለካፍ በደብዳቤ ቢጠይቅም ጥያቄው ካፍ ሳይቀበለው መቅረቱን ለማወቅ ችለናል። ካፍ እንደ ምክንያት ያቀረበው የተጫዋች ቁጥሩ ማነሱ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት መቐለ ሰባ እንድርታ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የማይሳተፍ ነገር ያከተመለት ሆኗል። በተጨማሪም ካፍ መቐለ በውድድሩ  አለመካፈሉን ተከትሎ ሌሎች ውሳኔዎችን በቀጣይ ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል።
© ሶከር ኢትዮጵያ