ባህርዳር ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አሳድጓል

ሁለት ተስፈኛ ተጫዋቾች ወደ ዋናው የጣና ሞገዶቹ ስብስብ አድገዋል፡፡

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ባህርዳር ከተማዎች ከሰዓታት በፊት በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከሲዳማ ቡና ጋር ጨዋታቸውን አድርገው 3-1 ያሸነፉ ሲሆን ረፋድ ላይ ለአስራ አምስት ቀናት ያህል በልምምድ ከክለቡ ጋር የነበሩት አማካዩ ጌታቸው ይበልጣል እና አጥቂው ይበልጣል አየለን ወደ ዋናው ቡድን መቀላቀል ችለዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ