ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን አማካይ ለዋናው ቡድኑ አስፈረመ

ከሀዋሳ የታዳጊ ቡድን የተገኘው ተስፈኛው አማካይ ወንድማገኝ ኃይሉ ለዋናው ቡድን ፈረመ፡፡

በቤቲንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን በመጪው ዓርብ ከሰበታ ከተማ ጋሮ የሚያደርገው ሀዋሳ አስራ አምስት ወጣቶችን ከተስፋ ቡድን በማደግ ክለቡን እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን አሁን ደግሞ ወጣቱን አማካይ ወንድማገኝ ኃይሉን ለሁለት ዓመት አስፈርሟል፡፡ በ2010 በሀዋሳ ከተማ ከ17 አመት በታች ቡድን ውስጥ በመጫወት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ የታየበት ተጫዋቹ በዛው ዓመት በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሴካፋ ቡድን ስብስብ አባል የነበረ ሲሆን ከብሔራዊ ቡድን መልስ ወደ ሀዋሳ ከ20 ዓመት በታች ቡድንን ተቀላቅሎ ሲጫወት ቆይቶ ወደ ሌላ ክለብ ያመራል ተብሎ ቢጠበቅም በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምርጫ በሁለት ዓመት ውል ለዋናው ክለብ ፊርማውን አኑሯል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ