ወላይታ ድቻ ከናይጄሪያዊው አጥቂ ጋር ተስማምቷል

ወላይታ ድቻ ናይጄሪያዊውን የቀድሞ የፋሲል አጥቂ ለማስፈረም ተስማምቷል።

የመሐል እና የመስመር አጥቂው ኢዙ አዙካ ድቻን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው። የህንዱ ክለብ ጃምሼድፑርን ከሁለት ዓመት በፊት ለቆ 2011 ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በፋሲል ከነማ እስከተሰረዘው የውድድር ዓመት ድረስ መጫወት የቻለው ኢዙ ከዐፄዎቹ ጋር ኮንትራቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ጥቂት ጊዜን ካለ ክለብ አሳልፎ ወደ ወላይታ ድቻ ለማምራት ቀደም ብሎ ንግግር ጀምሮ የነበረ ሲሆን አሁን ክለቡን ለመቀላቀል ተስማምቷል። የአጥቂ እጥረት ያለበትን ቡድን እንደሚያጠናክርም ይጠበቃል።

ወላይታ ድቻ ከኢዙ በፊት አስናቀ ሞገስ፣ ነፃነት ገብረመድህን፣ ዮናስ ግርማይ፣ ዳንኤል አጃይ፣ ዲዲዬ ለብሪ እና ጋቶች ፓኖምን ለማስፈረም የተስማማ ሲሆን ከስድስት ተጫዋቾች ጋር ደግሞ ተለያይቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ