ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የአስራ አምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ጨዋታን የተመለከቱ የመጨረሻ መረጃዎች እንድትጋሩ እንጋብዛለን።

በፋሲል ከነማ አንድ ለምንም ተሸንፈው ለዚህኛው ጨዋታ የቀረቡት የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሠልጣኝ ማሂር ዴቪድስ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው የዋንጫው ዕድል አሁንም እንዳላቸው በማመን ጨዋታዎችን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ላይ ጫና ማሳደር እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ። በሊጉ መሪ ከተረቱበት ቋሚ አሰላለፈም ጉዳት ያስተናገደውን አቤል ያለው በሮቢን ንግላንዴ ብቻ በመተካት ወደ ሜዳ ገብተዋል።

ከባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በተሻለ ለመንቀሳቀስ እንዳሰቡ የተናገሩት አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው በ14ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር ከሰበታ ከተማ ጋር አቻ ከተለያዩበት የመጀመሪያ አሰላለፍ ዘነበ ከበደን በአዲሱ ተጫዋቻቸው አወት ገብረሚካኤል በመለወጥ ለጨዋታው ቀርበዋል።

ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሀይለየሱስ ባዘዘው ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

ቡድኖቹ ወደ ሜዳ ይዘውት የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍ የሚከተለው ነው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ

22 ባህሩ ነጋሽ
14 ሄኖክ አዱኛ
15 አስቻለው ታመነ
6 ደስታ ደሙ
2 አብዱልከሪም መሐመድ
26 ናትናኤል ዘለቀ
16 የአብስራ ተስፋዬ
18 አቤል እንዳለ
27 ሮቢን ንጋላንዴ
28 አማኑኤል ገብረሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
6 አወት ገብረሚካኤል
14 ያሬድ ዘውድነህ
21 ፍሬዘር ካሣ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
8 ሱራፌል ጌታቸው
17 አስቻለው ግርማ
13 ኢታሙና ኬይሙኒ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ


© ሶከር ኢትዮጵያ