ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂውን ወደ ልምምድ መልሷል

ባሳለፍነው ወር ቅጣት ላይ የሰነበተው አጥቂ ዳግም ቡድኑን ተቀላቅሏል።

ጅማ ላይ በነበረው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአምስት ሳምንት ቆይታ በፈረሰኞቹ በኩል ሳላዲን ሰዒድ የዲሲፒሊን ጥሰት ፈፅሟል በሚል እገዳ እንደተጣለበት ይታወቃል። በእገዳውም እስከ መጋቢት 10 ድረስ ከዋናው ቡድን እንቅስቃሴ እንዲታገድ እንዲሁም የአምስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል እና ከተስፋ ቡድኑ ጋር አብሮ እንዲሰራ ተወስኖበት ነበር።

ቅዱስ ጊዮርጊሶች በቢሾፍቱ በሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ለድሬዳዋው ውድድር ዛሬ ዝግጅታቸውን በጀመሩበት ወቅት ሳላዲን ሰዒድ ከቡድኑ ጋር ተቀላቅሎ መሥራት መጀመሩን ሰምተናል።

በሌላ ዜና ለዕረፍት ወደ ሀገራቸው ያቀኑት ማሒር ዴቪድስ ዛሬ ቡድኑን ያዘጋጃሉ ተብሎ ቢጠበቅም ባለመገኘታቸው በቅርቡ ከታችኛው ቡድን እንዲመለስ የተደረገው አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ቡድኑን አሰርቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ