የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ሊገመገም ነው

በሦስት ከተሞች የተከናወነው የአንደኛ ዙር የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ግምገማ የሚደረግበት ቀን ታውቋል።

በሊጉ አክሲዮን ማኅበር የበላይ አስተዳደር የሚከናወነው የዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ላይ ጅማሮውን በማድረግ በጅማ አቆራርጦ ባህር ዳር ላይ የመጀመሪያውን ዙር ውድድር አከናውኗል። ለአስራ ስድስት ሳምንታት የዘለቀውን ውድድር ደካማ እና ጠንካራ ጎኖችንም ለመገምገም የሊጉ አክሲዮን ማኅበር የስብሰባ ጥሪ ለክለቦች መላኩ ተሰምቷል።

ማኅበሩ ለክለቦች በላከው ደብዳቤም ቅዳሜ መጋቢት 18 ወደፊት በሚገለፅ የመሰብሰቢያ ቦታ ተገኝተው የመጀመሪያውን ዙር ውድድር ከጠዋቱ 2:30 ጀምረው እንዲገመግሙ ጥሪ አስተላልፏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ