አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ባህር ዳር ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ

የምሽቱ ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድሞ እነዚህን መረጃዎች እንድትጋሩ ጋብዘናል።

ከፋሲል ከነማ ጋር ነጥብ የታጋሩት ባህር ዳሮች ለዛሬ ባደረጓቸው ሦስት ለውጦች መናፍ ዐወልን በሳሙኤል ተስፋዬ ፣ ፍፁም ዓለሙን በአፈወርቅ ኃይሉ እንዲሁም ምንይሉ ወንድሙን በባዬ ገዛኸኝ ቦታ ተጠቅመዋል።

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በኮቪድ ምክንያት አለመኖራቸውን የገለፁት የባህርዳር ምክትል አሰልጣኝ ታደሰ ጥላሁን የተለየ ዝግጅት ባያደርጉም ከባለፈው ጨዋታ ዕርማቶችን በማድረግ እና ተጫዋቾች ላይ ለውጥ በማድረግ ለጨዋታው እንደቀረቡ ተናግረዋል።

እንደተጋጣሚያቸው ሁሉ ሦስት ለውጦችን ያዱረጉት ድሬዳዋ ከተማዎች በዐወት ገብረሚካኤል ፣ በረከት ሳሙኤል እና ጁኒያስ ናንጄቦ ምትክ ያሬድ ዘውድነህ ፣ ፍሬዘር ካሳ እና ሪችሞንድ ኦዶንጎን ተጠቅመዋል።

አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ሊጉ ላይ ለመቆየት ያላቸው ብቸኛው አማራጭ ማሸነፍ በመሆኑ ሙሉ ሀሳባቸውን ውጤት ማግኘት ላይ አድርገው እንደሚገቡ ገልፀዋል
ጨዋታውን ትናንት በረዳትነት የተመለከትናቸው ማኑሄ ወልደፃዲቅ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

ቡድኖቹ ዛሬ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ባህር ዳር ከተማ

22 ፅዮን መርዕድ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
8 ሳምሶን ጥላሁን
14 ፍፁም ዓለሙ
18 ሳለአምላክ ተገኘ
7 ግርማ ዲሳሳ
25 ምንይሉ ወንድሙ

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
2 ዘነበ ከበደ
21 ፍሬዘር ካሳ
14 ያሬድ ዘውድነህ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
12 ዳንኤል ኃይሉ
8 ሱራፌል ጌታቸው
13 ኢታሙና ኬይሙኒ
99 ሙኅዲን ሙሳ
22 ሪችሞንድ ኦዶንጎ


© ሶከር ኢትዮጵያ