አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ወልቂጤ ከተማ

የአራተኛ ዙር የማሳረጊያ ጨዋታን ወቅታዊ መረጃዎች እንዲህ አሰናድተናል።

በሁለት ነጥብ ብቻ ተበላልጠው አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ወልቂጤ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከደቂቃዎች በኋላ የሚያደርጉት ፍልሚያ ጥሩ ፉክክር እንደሚታይበት ይታሰባል። በሦስተኛ ሳምንት ጨዋታ በኮልፌ ቀራኒዮ ሁለት ለምንም ተረተው ለዛሬው ጨዋታ የቀረቡት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ሦስት ነጥብ ካስረከቡበት ጨዋታ አምስት ለውጥ አድርገዋል። በዚህም አሠልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ግብ ጠባቂው ዘሪሁን ታደለን ጨምሮ ብሩክ ጌታቸው፣ ቢኒያም ትዕዛዙ፣ አደም አባስ እና ኤርሚያስ ኃይሉን ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ሜዳ በሚመለሰው ጫላ ድሪባ እንዲሁም ቢንያም ታከለ፣ አዲስ ነጋሽ፣ አንዳርጋቸው ይላቅ እና አቅሌሲያ ግርማ ተክተዋል።

በሦስተኛ ዙር የውድድሩ መርሐ-ግብር ከአዳማ ከተማ ጋር ተገናኝተው አንድ ነጥብ የተጋሩት ወልቂጤዎች ደግሞ አንድ ተጫዋች ብቻ ለውጠው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም አህመድ ሁሴን ፍሬው ሠለሞንን ተክቶ ጨዋታውን ጀምሯል።

ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሠ በሚመሩት ጨዋታ ላይ ቡድኖቹ የሚከተሉት ቋሚ አሰላለፍ የሚከተለው ነው።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ

18 ቢንያም ታከለ
2 አዲስ ነጋሽ
13 ፍራኦል መንግሥቱ
21 ወልደአማኑኤል ጌቱ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ
16 ሀብታሙ ጥላሁን
6 እንዳለ ዘውገ
12 አቅሌሲያ ግርማ
19 ሳሙኤል ታዬ
3 አቤል ታሪኩ
17 ጫላ ድሪባ

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
12 ተስፋዬ ነጋሽ
15 ዮናስ በርታ
19 ዳግም ንጉሴ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
14 አብዱልከሪም ወርቁ
18 በኃይሉ ተሻገር
8 አቡበከር ሳኒ
7 አሜ መሐመድ
10 አህመድ ሁሴን