ሀዋሳ ከተማ ተከላካይ አስፈርሟል

በቅርቡ አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን የተቀጠረው ሀዋሳ ከተማ ተከላካይ መስመር ተጫዋች አስፈርሟል።

አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን በሁለት ዓመት የውል ዕድሜ በቅርቡ በይፋ የቀጠረው ሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ ጎራ በማለት አንድ አዲስ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ማስፈረሙን ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው መረጃ ገልጿል፡፡ ክለቡ የተቀላቀለው አዲስ ፈራሚም ፀጋሰው ድማሙ ሆኗል፡፡ 

ይህ የመሐል የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ረዘም ያሉ ዓመታትን በትውልድ ከተማው ክለብ ሀድያ ሆሳዕና በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን በተለይ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ካሳየው ድንቅ አቋም አንፃር በበርካታ ክለቦች ተፈላጊ መሆን ቢችልም በሁለት ዓመት የውል ኮንትራት መዳረሻው ሀይቆቹ ሆኗል፡፡

የፀጋሰው ድማሙ መፈረም በቅርቡ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ምኞት ደበበን ክፍተት እንደሚሸፍን ይጠበቃል።