አቡበከር ናስር ወደ ሞሮኮ ሊያመራ ይሆን ?

አቡበከር ናስር ወደ ውጪ ሀገር ክለብ ሊያመራ ስለመሆኑ እየተነገረ ይገኛል።

ዘንድሮ በኢትዮጵያ እግርኳስ ደምቆ የታየው አበቡበከር ናስርን የተለያዩ የውጭ ሀገር ክለቦች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ለተጫዋቹ ባለቤት ኢትዮጵያ ቡና ጥያቄዎች እየቀረቡ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወቃል።

ሀገራዊ ጥሪ ቀርቦለት በግል ጉዳይ ምክንያት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የማይገኘው አቡበከር ዛሬ ከቡድኑ ጋር መቀላቀሉን ከሰዓታት በፊት ዘግበን ነበር። አሁን ባገኘነው መረጃ መሠረት አቡበከር ከኢትዮጵያ ውጭ ወጥቶ ለመጫወት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የክለቡን ስም ለጊዜው ማወቅ ባንችልም የኢትዮጵያ ቡና አመራሮች እና አንድ የሞሮኮ ክለብ ወኪል በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ድርድር እያደረጉ እንደሆነና ከስምምነት የሚደርሱ ከሆነ ወደ ስፍራው ሊጓዝ እንደሚችል አውቀናል።

በሌላ ዜና ዛሬ አስር ሰዓት የክለቡ ሥራ አመራር ቦርድ በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ስብሰባ እንደሚያደርግ ሰምተናል።