ናሚቢያዊው አጥቂ ወደ ሰበታ ከተማ አምርቷል

የተጠናቀቀው የውድድር ዘመንን በድሬዳዋ ከተማ ያሳለፈው አጥቂ ወደ ሰበታ ከተማ እንደሚያመራ ተረጋግጧል።

በአሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራው እየተመሩ ስብስባቸውን እያጠናከሩ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊት ጁኒያስ ናንጄቦን የግላቸው ማድረጋቸው ታውቋል። በኮቪድ-19 ምክንያት በተሰረዘው የ2012 የውድድር ዘመን ወልዋሎ ዓ/ዩን በመቀላቀል ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ናንጄቦ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ደግሞ ወደ ድሬዳዋ ከተማ በማምራት ተጫውቶ ነበር። ከብርቱካናማዎቹ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎም ዛሬ ወደ ሰበታ ከተማ በአንድ ዓመት ውል ማምራቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በሀገሩ የሚገኘው ፈጣኑ አጥቂ ናንጄቦ በፌዴሬሽን በኩል ያለውን ዝውውር ያጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ክለቡን እንደሚቀላቀል ሰምተናል።