ሰበታ ከተማ ዝግጅት የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

አሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ከሾሙ በኋላ በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ያመጡት ሰበታ ከተማዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል።

ለ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዝግጅቱን የአሠልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን በማውጣት እና ይመጡኑኛል ያላቸውን አሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በመሾመረ የጀመረው ሰበታ ከተማ ከዛም ፊቱን ወደ ተጫዋቾች ዝውውር በማዞር አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም ነበር። ከአዳዲሶቹ ተጫዋቾች በተጨማሪ የጥቂት ነባሮችንም ውል ያደሰው ክለቡ በዛሬው ዕለት አሠልጣኝ ዳንኤል ገብረማርያምን ምክትል አድርጎ ቀጥሮ እንደነበር ከሰዓታት በፊት ዘግበን ነበር።

ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሠረት ደግሞ ክለቡ ነገ ረፋድ ላይ የጤና ህክምና እና የኮቪድ 19 ምርመራን የሚያደርግ ይሆናል። በሀዋሳ ሐሮኒ ኢንተርናሽናል ሆቴል ማረፊያውን ያደረገው ክለቡም ከጠዋቱ ምርመራ በኋላ ከሰአት በይፋ ልምምድ እንደሚጀምር ታውቋል።