ዲ ኤስ ቲቪ ለፕሪምየር ሊጉ አሠልጣኞች ስልጠና ሊሰጥ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የምስል ባለ መብት ዲ ኤስ ቲቪ ለአስራ አንድ ቀናት የሚቆይ ሥልጠና ለሊጉ አሠልጣኞች ሊሰጥ መሆኑ ታውቋል።

ከ2013 ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ዓመታት የሊጉን የምስል መብት ዳጎስ ባለ ገንዘብ የገዛው ዲ ኤስ ቲቪ የፕሪምየር ሊጉን ገፅታ ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል። ከሳምንታት በፊት ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ጋር በመሆን ለሊጉ አመራሮች ሥልጠና የሰጠው ተቋሙ አሁን ደግሞ ቀድሞ ቃል በገባው መሠረት ለአሠልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ሊሰጥ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ከመስከረም 17-28 ድረስ በሚሰጠው ሥልጠና ላይ እያንዳንዱ ክለብ ሁለት ሁለት አሠልጣኞችን (ዋና እና ረዳት) እንዲልክ እንደሚደረግ የሰማን ሲሆን ሥልጠናውም ተሳታፊዎችን በሁለት ቡድኖች ከፍፍሎ እንደሚሰጥ ተነግሮናል። ይህንን የሙያ ማሻሻያ ስልጠናም ከሆላንድ የሚመጡ ባለሙያዎች እንደሚሰጡት ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።