ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል

በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ሩዋንዳን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለጨዋታው ይዞት የሚገባው አሰላለፍ ታውቋል።

ከሳምንት በፊት ሩዋንዳ ላይ 4-0 ያሸነፈው ብሔራዊ ቡድኑ ለመልሱ ጨዋታ በአዲስ አበባ እና ባህር ዳር ሲዘጋጅ የቆየ ሲሆን ዛሬ 10፡00 ላይ በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል። ለዚህ ጨዋታም አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚጠቀሙባውን ተጫዋቾች የለዩ ሲሆን ሩዋንዳ ላይ ካሸነፈው ስብስብ በሀዘን ምክንያት ከስብስቡ ውጪ የሆነችው ብዙዓየሁ ታደሰ በነፃነት ፀጋዬ ከመተካቷ ውጪ ሌሎች ላይ ለውጥ አልተደረገም።

አሰላለፍ፦

እየሩሳሌም ሎራቶ

ነፃነት ፀጋዬ – ብርቄ አማረ – ቤተልሔም በቀለ – ናርዶስ ጌትነት (አ)

ማዕድን ሳህሉ – ገነት ኃይሉ – መሳይ ተመስገን

አረጋሽ ካልሳ – ቱሪስት ለማ – ረድኤት አስረሳኸኝ