ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋቾች አስፈርሟል

የቀድሞው አሰልጣኙ አላምረው መስቀሌን በድጋሚ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው ሀላባ ከተማ ታዳጊዎች እና አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ ይገኛል።

ሳምሶን ቆልቻ ከፈራሚዎቹ መካከል ነው። የፊት መስመር ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በወላይታ ድቻ እና ጅማ አባጅፋር የተጫወተ ሲሆን ዐምና ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ጅማ አምርቶ ከተጫወተ በኋላ ለዘንድሮ የውድድር ዓመት ማረፊያው በርበሬዎቹ ቤት ሆኗል።

የቀድሞ የሀላባ ከነማ ተጫዋቾች የነበሩት ፍሬው ኪዳኔ እና ተመስገን ይልማ እንዲሁም ሄኖክ ተረፈ፣ በተከላካይ ክፍል ከስልጤ ወራቤ ንስሀ ታፈሰ እና ተካልኝ ጂንባ ከከፋ ቡና፣ በግብ ጠባቂ ስፍራ ከከፋ ቡና ደግነት ዳቆሮ የአሰልጣኝ አላምረው መስቀሌ ምርጫ በመሆን ቡድኑን ተቀላቅለዋል።

በርበሬዎቹ ከአዲስ ፈራሚዎች በተጨማሪ ሸምሱ መሀመድ አታክንግ፣ ጀሚል ታምሬ፣ ሙባረክ ከድር፣ አብዱልአዚዝ አብደላ፣ በኃይሉ ንጉሤ፣ አብዲ ጀማል፣ ፍቅረየሱስ ጸሐይ፣ ስጦታው፣ አድኖ አባተ ወደ ዋናው ቡድን ያደጉ ተጨዋቾች ናቸው።

ግብ ጠባቂው ንጉሥ ሙሉጌታ፣ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ቴዎድሮስ ወልዴ እና አማክዩ ሠዒድ ግርማ ደግሞ ለ1 ዓመት ውል ማደሳቸውን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።