የፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጉባኤ እና ምርጫ የሚደረግበት ወር እና ቦታ ታውቋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ ተደርጎ ሲጠናቀቅ ቀጣዩ አስቸኳይ እንዲሁም ደግሞ የምርጫ ጉባኤ የሚደረግበት ወር እና ቦታ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ዓመታዊ 13ኛ መደበኛ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ ተከናውኖ ከሰዓታት በፊት ፍፃሜውን ሲያገኝ በቀጣዩ የአስቸኳይ እና የምርጫ ጉባኤ የሚደረግበት ወር እና ቦታ ተለይቶ ታውቋል፡፡ በዚህም መሠረት የፊታችን መጋቢት ወር ላይ የፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚደረግ ሲሆን የፌድሬሽኑን ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት በተጨማሪነትም የስራ አስፈፃሚ አባላትን ለመምረጥ የሚደረገው ጉባኤ ደግሞ በሰኔ ወር ጎንደር ከተማ ላይ እንደሚደረግ ተወስኗል፡፡