​ድሬዳዋ የሊጉን ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ያለችበትን ግብዣ ምሽት ላይ አከናውናለች

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ከ10ኛ ሳምንት ጀምሮ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን እያስተናገደች የምትገኘው ድሬዳዋ ከተማ እንግዶቿን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የእራት ግብዧ መርሐ-ግብር አከናውናለች።

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በኋላ የቀጠለውን የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግን ከ10ኛ ሳምንት ጀምሮ እያስተናገደች የምትገኘው ድሬዳዋ ከተማ ዛሬ አመሻሽ እንግዶቿን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት በራስ ሆቴል ግብዧ አከናውናለች። የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞን ጨምሮ የ16ቱ ክለብ ተወካይ የቡድን መሪዎች፣ አሠልጣኞች፣ የዲ ኤስ ቲ ቪ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በራስ ሆቴል በተከናወነው የእራት ግብዧ ላይ ታድመዋል።


ይጀመራል ተብሎ ከታሰበው ዘለግ ያሉ ደቂቃዎችን አርፍዶ የተጀመረው መርሐ-ግብር ላይ በቅድሚያ የከተማው ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዋናነትም ሁሉም ከተማውን እንደ ቤቱ እንዲያይ እና ከፀጥታ ጀምሮ ከፍተኛ ስራዎች መሰራታቸውን አውስተው እንግዶቹን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል። በማስከተል ደግሞ የአክሲዮን ማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ንግግር አድርገዋል። ሰብሳቢውም “ከፓውዛ ጀምሮ የተሰሩ ስራዎች እጅግ የሚደነቁ ናቸው። ዓምና ድሬዳዋ ላይ ችግር ገጥሞን ነበር። ግን ችገሩ ሰው ሰራሽ ሳይሆን ተፈጥሮዋዊ ነበር። ያለ ወቅቱ ዝናብ ዘንቦ። ከዚህም መነሻነት ብዙሀኑ ነቄፌታ ሲሰነዝር ነበር። ዘንድሮ ወደዚህ ከተማ ስንመጣ ከተፈጥሮዋዊ ችግሮች ውጪ ዓምና የተከሰቱት ጥቃቅን ክፍተቶች እንደማይደገሙ አውቀን ነው። ሊጉም በደመቀ ሁኔታ እየተከናወነ ነው።


“ከሀዋሳ ከተማ ቀጥለን የምንሄድባቸው ከተሞች ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ስለነበረብን 9 ሳምንታተን እዛ (ሀዋሳ) ለማሳለፍ ተደገናል። አሁን እንዳያችሁት በጥሩ ሁኔታ ድሬዳዋ ላይ እየተደረገ ነው። ብዙ ጎሎችም እየተስተናገዱ ነው። ይህ ከሆነባቸው ምክንያቶች አንደኛው ደግሞ የስታዲየሙ ምቹነት ነው። በእኛ ድሬዳዋ የሊጉን ጨዋታዎች በቋሚነት የምታስተናገድ ቀዳሚ ከተማ ነች።” ካሉ በኋላ በቀጣይ ዓመት ሊጉ ሲጀምር ድሬዳዋ ላይ እንደሚሆን አመላክተው ንግግራቸውን ቋጭተዋል።

ከሁለቱ አመራሮች ንግግር በኋላ የእራት መርሐ-ግብር ተከናውኖ ዝግጅቱ ፍፃሜውን አግኝቷል።