ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ታውቋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

የ2014 የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት የሚከናወንበት እንዲሁም ውድድሩ የሚጀመርበት ቀን ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር ከሚደረጉ ውድድሮች መካከል የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ይጠቀሳል፡፡ ከዕድሜ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ቅሬታ የሚነሳበት ይህ ውድድር ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተወሰነ ረገድ መሻሻሎች የታየበት ሲሆን የዘንድሮውም ውድድር ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚደረግ ሰምተናል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የነበሩ አስራ አራት ክለቦች አሁንም በውድድሩ ላይ የሚካፈሉ ሲሆን ተጨማሪ አዳዲስ አምስት ክለቦች ተሳታፊ ለመሆን ምዝገባ እና የኤም አር አይ ምርመራን እንዳደረጉ ተገልጿል፡፡ በሁለት ምድብ ተከፍሎ በሁለት የተመረጡ ከተሞች እንደሚደረግ የሚጠበቀው ይህ ሊግ የካቲት 5 የዕጣ ማውጣት መርሀግብሩ ከተከወነ ሰባት ቀናቶች በኋላ ማለትም የካቲት 12 ውድድሩ እንደሚጀመር ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች፡፡