​የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር የሚጀመርበት ቀን ታውቋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

አስራ አራት ክለቦችን ተሳታፊ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች መቼ እንደሚጀመር ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ስር ከሚዘጋጁ ውድድሮች መካከል የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር ይጠቀሳል፡፡ አስራ አራት ክለቦችን በአንድ ምድብ አቅፎ የመጀመሪያውን ዙር የአስራ ሦስት ሳምንታት ጨዋታዎች በባቱ እና ሀዋሳ ከተሞች ሲያከናውን ሰንብቶ ከቀናቶች በፊት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማን በመሪነት ቦታ በማስቀመጥ መገባደዱ ይታወሳል፡፡ ምንም እንኳን ፌድሬሽኑ የሁለተኛው ዙር ውድድር የሚደረግበትን ከተማ ይፋ ባያደርግም ጨዋታዎቹ ልክ እንደ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ በተመሳሳይ ቀን መጋቢት 24 እንደሚጀምር ለክለቦች በላከው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡

በተያያዘ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የአራት ሳምንት ጨዋታዎች በሀዋሳ ከተማ ከተደረጉ በኋላ ለኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እና ዝግጅት በሚል መቋረጡ የሚታወቅ ነው። ውድድሩም መጋቢት 24 እንደሚጀምር በዘገባችን ከዚህ ቀደም ጠቁመን የነበረ ሲሆን ቀጣይ የአንደኛው ዙር ቀሪ ሙሉ ጨዋታዎች በባህርዳር ከተማ እንዲደረግ መወሰኑም ታውቋል።