ኢትዮጵያን ያሸነፈችው ካሜሩን ፣ ናይጄርያ እና ጋና ለ17 አመት በታች ሴቶች አለም ዋንጫ አልፈዋል

ከሴፕቴምበር 30 – ኦክቶበር 21,2016 ጆርዳን ላይ ለሚስተናገደው ከ17 አመት በታች ሴቶች የአለም ዋንጫ አፍሪካን የሚወክሉ 3 ሃገራት ታውቀዋል፡፡ በሴቶች እግርኳስ የአፍሪካ የበላይነታቸውን በተደጋጋሚ ያስመሰከሩት የምዕራብ አፍሪካ ሃገራትም በማጣርያው የበላይ ሆነዋል፡፡

በመጀመርያው የማጣርያ ዙር ኢትዮጵያን በድምር ውጤት 3-3 (ካሜሩን በመለያ ምቶች አሸንፋለች) በመርታት ወደ ተከታዩ የማጣርያ ዙር ያለፈችው ካሜሩን ግብፅን በድምር ውጤት 6-1 በማሸነፍ የአለም ዋንጫ ትኬቷን ቆርጣለች፡፡ ካሜሩን በመጀመርያው ጨዋታ በሜዳዋ 2-1 ያሸነፈች ሲሆን በመልሱ ጨዋታ ከሜዳዋ ውጪ ባልተጠበቀ ሁኔታ 4-0 ማሸነፍ ችላለች፡፡

ጋና በሞሮኮ ላይ የግብ ናዳ በማውረድ ወደ አለም ዋንጫው አልፋለች፡፡ ከሜዳዋ ውጪ 4-0 በማሸነፍ ወደ አክራ የተመለሰችው ጋና በመልሱ ጨዋታ 6-0 በማሸነፍ በ10-0 ድምር ውጤት አልፋለች፡፡

ሌላዋ የምዕራብ አፍሪካ ሃገር ናይጄርያ ደቡብ አፍሪካን በመርታት በእያንዳንዱ የአለም ዋንጫዎች ላይ የመሳተፍ ሪከርዷን አስጠብቃለች፡፡ ሌጎስ ላይ 6-0 አሸንፋ ወደ ጆሃንስበርግ ያቀናችው ናይጄርያ 1-0 በማሸነፍ በ7-0 ድምር ውጤት የአለም ዋንጫውን ተቀላቅላለች፡፡

ፎቶ © CAF
ፎቶ © CAF

የአለም ዋንጫው ተሳታፊ ሃገራት የሚከተሉት ናቸው

ኮንካካፍ (ሰሜን እና መካከለኛው አሜሪካ ፣ 3)

ካናዳ ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ፣ ሜክሲኮ

ኮሜቦል (ደቡብ አሜሪካ ፣ 3)

ቬኔዝዌላ ፣ ብራዚል ፣ ፓራጓይ

ካፍ (አፍሪካ ፣ 3)

ጋና ፣ ናይጄርያ ፣ ካሜሩን

ኤኤፍሲ (ኤሽያ ፣ 3)

ጆርዳን ፣ ሰሜን ኮርያ ፣ ጃፓን

ኦኤፍሲ (ኦሽንያ ፣ 1)

ኒውዝላንድ

ዩኢኤፍኤ (አውሮፓ ፣ 3)

የማጣርያ ጨዋታዎች አልተጠናቀቁም፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *