ጋቦን 2017 : ኢትዮጵያ ከ አልጄርያ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከአአ ስታድየም

ኢትዮጵያ 3-3 አልጄሪያ 

29′ 48′ ጌታነህ ከበደ, 64′ ዳዊት ቃዱ

43′ ኢስላም ስሊማኒ, 61′ አይሳ ሜንዲ, 85′ ፋውዚ ጉላም

የቀጥታ ፅሁፍ ስርጭት ከሶከር ኢትዮጵያ 


ተጠናቀቀ!!!

ጨዋታው 3-3 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀቀ

90′ መደበኛው ክፍለጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አልጄርያ

87′ ያቺን ብራሂሚ ወጥቶ አድላኔ ጎውድሌራ ገብቷል፡፡

85′ ጎልልል አልጄርያ 

ፋውዚ ጉላም የፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

ፍፁም ቅጣት ምት 

84′ አንተነህ ብራሂሚ ላይ በሰራው ጥፋት የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ

81′ የመስመር አጥቂው ራምኬል ወጥቶ የመስመር ተከላካዩ አብዱልከሪም መሃመድ ገብቷል፡፡

80′ አልጄርያዎች ደካማ እንቅስቃሴ እያሳዩ ቢሆንም ወደ ኢትዮጵያ የግብ ክልል ሲደርሱ አስፈሪ ናቸው፡፡

77′ ራምኬል ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ኤልያስ በግንባሩ ገጭቶ ቢሞክርም ሬይስ ይዞበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አልጄርያ

76′ ጨዋታው ላይ ጠፍቶ የዋለው ሶፊያን ፌጉይሊ ወጥቶ ራሺድ ጋዜል ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ

70′ በጨዋታው ድንቅ እንቅስቃሴ ያሳየው ታደለ መንገሻ ወጥቶ ኤልያስ ማሞ ገብቷል፡፡

64′ ጎልል!!!! ኢትዮጵያ

ጌታነህ ከበደ ወደ ግብ አክርሮ የመታውን ኳስ ሬይስ ሲመልሰው ዳዊት ፍቃዱ አግኝቶት ኢትዶጵያን በድጋሚ መሪ ያደረገ ግብ አስቆጥሯል፡፡

63′ ኢስላም ስሊማኒ ያሻማውን ኳስ ብራሂሚ ሞክሮ አቤል አውጥቶበታል፡፡ አስደንጋጭ ሙከራ ነበር፡፡

61′ ጎልልል!!! አልጄርያ

አይሳ ሜንዲ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አልጄርያ

58′ ዋሊድ መስሎብ ወጥቶ ያሲን ቤንዚያ

54′ ሽመልስ ከቅጣት ምት የሞከረውን ኳስ ሬይስ አውጥቶታል፡፡

52′ ጌታነህ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ዳዊት ፍቃዱ ጋር ሳይደርስ ሬይስ አውጥቶታል፡፡

50′ ጋቶች ፓኖም ከርቀት የሞከረውን ኳስ ሬይስ ቦልሂ ይዞበታል፡፡

48′ ጎልልል!!!! ጌታነህ ከበደ 

ጌታነህ ከበደ ከታደለ በግሩም ሁኔታ የተሻገረለትን ኳስ በግሩም አጨራረስ ወደ ግብነት ቀይሮታል

ተጀመረ

2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል

የእረፍት ሰአት ቅያሪ

በሃይሉ አሰፋ ወጥቶ ዳዊት ፍቃዱ ገብቷል



 

እረፍት!!!

የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

43′ ጎልልል!!!! አልጄርያ

ኢስላም ስሊማኒ ከዋሊድ መስሎብ በግሩም ሁኔታ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ  በመግጨት አልጄርያን አቻ አድርጓል፡፡

ቢጫ ካርድ – አልጄርያ

42′ ኢስላም ስሊማኒ በአሉላ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

40′ ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ ከአርቡ ጨዋታ የተለየ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ በኳስ ቁጥጥርም የተሻሉ ሆነዋል፡፡

31′ ስሊማኒ ከማህሬዝ የተቀበለውን ኳስ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

29′ ጎልልል!!! ኢትዮጵያ

ጌታነህ ከበደ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ወደ ግብነት ለውጦታል፡፡

25′ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተደጋጋሚ ወደ አልጄርያ የግብ ክልል ቢቀርቡም ግልፅ የግብ ማግባት አጋጣሚዎችን መፍጠር አልቻለም፡፡

20′ ጌታነህ ከቅጣት ምት በቀጥታ የሞከረውን ኳስ ሬይስ ምቦሊ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

18′ ሽመልስ በቀለ ያሻገረውን ኳስ ተጠቅሞ ጌታነህ ግብ ማለፍ ቢችልም ኳሷን ሳይደርስባት ቀርቷል፡፡

15′ የጨዋታው ፍጥነት እንደአጀማመሩ መሆን አልቻለም፡፡ አልጄርያዎች ጨዋታውን በሚፈልጉት ፍጥነት ለማስኬድ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

10′ ፌጉይሊ ያሻማውን ኳስ አቤል ለመያዝ ሲሞክር ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡ የማዕዘን ምቱ በኢትዮጵያ ተጫዋቾች ተመልሷል፡፡

5′ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በፈጣን ማጥቃት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን 3 የማዕዘን ምቶችም አግኝቷል፡፡ 1 ኢላማውን የጠበቀ ሙከራም ማድረግ ችሏል፡፡

4′ ራምኬል ሎክ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

2′ ጋቶች ፖኖም ከርቀት የሞከረውን ኳስ ሬይስ አድኖበታል፡፡

ተጀመረ

ጨዋታውን አልጄርያዎች ጀምረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከግራ ወደቀኝ ስታጠቃ አልጄርያ ከቀኝ ወደ ግራ ታጠቃለች


 

የኢትዮጵያ ቋሚ አሰላለፍ (4-2-3-1)

1. አቤል ማሞ

6. አሉላ ግርማ – 15. አስቻለው ታመነ – 4. አንተነህ ተሰፋዬ – 11. ሱሌማን መሃመድ

7. ጋቶች ፓኖም – 16. ታደለ መንገሻ

14. በኃይሉ አሰፋ – 18. ሽመልስ በቀለ (አምበል) – 10. ራምኬል ሎክ

9.ጌታነህ ከበደ

ተጠባባቂዎች

12. ለአለም ብርሃኑ ፣ 3. ያሬድ ባየህ ፣ 5. ወንድይፍራው ጌታሁን ፣ 2. ተካልኝ ደጀኔ ፣ 13. አብዱልከሪም መሃመድ ፣ 8. ኤልያስ ማሞ ፣ 17. ዳዊት ፍቃዱ

የአልጄርያ ቋሚ አሰላለፍ (4-2-3-1)
1.ቦልሂ ሬይስ

18.ሜህዲ ዜፋኔ – 2.አይሳ ማንዲ – 12.ካርል ሜጃኒ (አምበል) – 3.ፋውዚ ጉላም

6. ዋሊድ መስሎብ – 8.ሳፊር ታይደር

10.ሶፊያን ፌጉይሊ – 7.ሪያድ ማህሬዝ
– 11.ያቺን ብራሂሚ

13.ኢስላም ስሊማኒ

ተጠባባቂዎች

4. ሜህዲ አቤይድ ፣ 5. ሂቻም ቤልካውሪ 9. ያሲን ቤንዚያ 14. ሪያድ ቦዴቦውዝ 15. ራሺድ ጋዜል 16. ማሊክ አስላህ 17. አድላኔ ጉዌድዮራ



10:57 የሁለቱም ሀገራት ብሄራዊ መዝሙር ተዘምሯል፡፡ በአሁኑ ሰአት ሰላምታ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ፡፡

10:55 ሁለቱ ቡድኖች ፣ ዳኞች ፣ እንግዶች ወደ ሜዳ እየገቡ ይገኛሉ፡፡

10:45 ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡ ስታድየሙ ሙሉ ለሙሉ በተመልካች ተሞልቷል፡፡ 

PicsArt_1459257962340

PicsArt_1459257914952

10:20 በአሁኑ ሰአት ሁለቱም ቡድኖች ከመልበሻ ክፍል ወጥተው ሰውነታቸውን በማፍታታት ላይ ይገኛሉ፡፡ ተመልካቹም ሪያድ ማህሬዝ ወደ ሜዳ ሲገባ በጭብጨባ ተቀብለውታል፡፡

09:30 የሁለቱም ቡድን አባላት ስታድየም ደርሰው ወደ መልበሻ ክፍል ያመሩ ሲሆን በብሊዳው ጨዋታ በሀዘን ምክንያት ያልነበሩት ረዳት አሰልጣኙ ፋሲል ተካልኝ ዛሬ ከቡድኑ ጋር ተገኝተዋል፡፡

ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞችም ሜዳውን እና መረቡን በመፈተሽ ላይ ይገኛሉ፡፡

PicsArt_1459252430882
08:45 አአ ስታድየም በአሁኑ ሰአት

 

የቡድን ዜናዎች

ሽመልስ በቀለ ቡድኑን በአምበልነት ይመራል፡፡ አስራት መገርሳ (ጉዳት) ፣ ታሪክ ጌትነት (ጉዳት) እና ቢንያም በላይ ከ18 ስብስቡ ውጪ ሲሆኑ ታደለ መንገሻ ፣ አንተነህ ተስፋዬ ፣ አቤል ማሞ እና ሱሌማን መሃመድ ከአርቡ ጨዋታ የተለወጡ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ጨዋታውን የሚመሩ ዳኞች 

ዋና ዳኛ – ዳቪስ ኦጋንቼ ኦምዌኖ (ኬንያ)

ረዳት ዳኞች – ማራዋ ራንጌ (ኬንያ) እና ጊልበርት ቼሮይት (ኬንያ)

ማልያ

ኢትዮጵያ – አረንጓዴ – ቢጫ- ቀይ

አልጄርያ – ነጭ – ነጭ – ነጭ

ቀጥታ ስርጭት

ሀገር ውስጥ ስርጭት – EBC

ከሰሃራ በታች ስርጭት – Super Sport

አረብ ሃገራት – BeIn Sport

የመግብያ ዋጋ 

ክቡር ትሪቡን – 500 ብር

ጥላ ፎቅ – 300 ብር

ከማን አንሼ በወንበር – 100

ከማን አንሼ ካለ ወንበር – 50

ካታንጋ – 20

ሚስማር ተራ – 10

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *