‹‹ በሽንፈቱ የደረሰብንን የስነልቦና ጉዳት እና የጉዞ ድካም ተቋቁመን ጥሩ ተጫውተናል ›› ታደለ መንገሻ 

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ አስር 4ኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አልጄርያን አስተናግዶ 3-3 ተለያይቷል፡፡ በጨዋታው ጌታነህ ላስቆጠራቸው ግቦች ትልቅ ሚና የተወጣው ታደለ መንገሻ በአልጄርያው አሰልጣኝ ክርስትያን ጎርኩፍ ጭምር የጨዋታው ኮከብ ያሰኘውን ብቃት አሳይቷል፡፡

ታደለ ከጨዋታው በኀላ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት ከከባድ ሽንፈት እና አድካሚ ጉዞ በኋላ ጥሩ ጨዋታ እንዳደረጉ ተናግሯል፡፡

‹‹ ጨዋታው ከሞላ ጎደል በጣም ጥሩ ነበር፡፡ በስነልቦናው ረገድ ብንጎዳም በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ግን የተቻለንን ለማድረግ ነበር የነባነው፡፡ ጥሩ እቅስቃሴም አድርገናል፡፡ የ7-1 ሽንፈቱ በስነልቦናችን ላይ ጫና ፈጥሮብን ነበር፡፡ ከዛ በተጨማሪ ደግሞ በጉዞው ላይ ፌዴሬሽናችን ማድረግ የሌለበትን ነገር ነው ያደረገው፡፡ አልጄርያዎች በቀጥታ በረራ 7 ሰአት ተጉዘው ነው አዲስ አበባ የመጡት፡፡ እኛ ግን 20 ሰአት ነው የተጓዝነው፡፡ ይህ ትልቅ ተጽእኖ ነው የፈጠረብን፡፡ ነገር ግን ያንን ተቋቁመን ጥሩ ውጤት አስመዝግበናል ብዬ ነው የማስበው፡፡ አቻ የወጣነውም በመጨረሻ ደቂቃ በተቀጠረ ግብ ነው፡፡›› ብሏል፡፡

ታደለ አያይዞም ራሱን ከአልጄርያ ተጫዋቾች አሳንሶ ወደ ሜዳ አለመግባቱ በዋታው ጥሩ እንዲንቀሳቀስ እንዳደረገው ጠቁሟል፡፡ ‹‹ በእርግጥ የአልጄርያ ተጫዋቾች ትልልቅ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ በሜዳ ላይ በሚታየው እንቅስቃሴ ግን ከነሱ እንደማላንስ ራሴን አሳምኜ ነው የገባሁት፡፡ ››

PicsArt_1459283537541

በዘንድሮው የውድድር ዘመን አርባምንጭ ከተማን የተቀላቀለው ታደለ መንገሻ በአሰልጣኝ ዮሃነስ ሳህሌ ዘመን ለመጀመርያ ጊዜ በቋሚ አሰላለፉ ውስጥ ተካቶ ተጫውቷል፡፡ ታደለ ለወደፊቱም የብሄራዊ ቡድ ቦታውን ለማስከበር ጠንክሮ እንደሚሰራ ገልጧል፡፡ እስካሁን በብሄራዊ ቡድን ቋሚ ተሰላፊ መሆን ያቻልኩት አሰልጣኞች ይዘው ለሚገቡት የተለያዩ ሲስተሞች አመቺ ስላልሆንኩ ይሆናል፡፡ ከዚህ በኋላ ላለው ደግሞ ጠንክሬ በመስራት ለሃገሬም አንድ ነገር እሰራለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡›› ብሏል፡፡

ታደለ በመጨረሻም የብሄራዊ ቡድናችን የማለፍ ተስፋ እንዳላከተመ ይናገራል፡፡ ‹‹ የማለፍ ተስፋችን አሁንም አለ፡፡ በአንዳንዶቹ ምድቦች ዝቅተኛ ነጥብ ይዘው የሚመሩ አሉ፡፡ ከኛ የሚጠበቀው በቀሪዎቹ 2 ጨዋታዎች ውጤት ለማስመዝገብ ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ ነው፡፡ ››

PicsArt_1459283475203

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *