የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮን ግብፅ ናይጄሪያን አሌሳንድሪያ ላይ 1-0 በማሸነፍ ከ2010 በኃላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለመመለስ ተቃርባለች፡፡ በምድብ 7 ቻድ በገንዘብ ዕጥረት ምክንያት ራሷን በማግለሏ ምክንያት የማለፍ እድሏ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ የነበረው የ2013 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ ከማጣሪያው ውጪ ሆናለች፡፡
የአል አሃሊው የመስመር አማካይ ረመዳን ሶብሂ የፈርኦኖቹን የድል ግብ በ65ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር ቪክቶር ሞሰስ በ84ኛው ደቂቃ ከረጅም ርቀት ወደ ግብ የላካት ኳስ የግቡን አግዳሚ መልሳበታለች፡፡ የ1-0 ውጤቱን ተከትሎ ነጥቧን ወደ ሰባት ያሳደገችው ግብፅ አፍሪካ ዋንጫው ለመግባት ተቃርባለች፡፡
በምድብ 10 ከኢትዮጵያ ጋር የተደለደሉት ሌሴቶ እና ሲሸልስ ማሴሩ ላይ ተጫውተው ሌሴቶ 2-1 ማሸነፍ ችሏለች፡፡ ቱሚሎ ኩትላንግ ሌሱቶ የማሸነፊያውን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ይህ ድል ሌሴቶ በምድብ ማጣሪያው ያሳካቸው የመጀመሪያ ነጥብ ነው፡፡
ምድብ 10ን አልጄሪያ በ10 ነጥብ ስትመራ ኢትዮጵያ በ5 ትከተላለች፡፡
የማክሰኞ ውጤቶች፡-
ኢትዮጵያ 3-3 አልጄሪያ
ዩጋንዳ 0-0 ቡርኪና ፋሶ
ግብፅ 1-0 ናይጄሪያ
ሱዳን 1-1 ኮትዲቯር
ኒጀር 1-2 ሴኔጋል
ማላዊ 1-2 ጊኒ
አንጎላ 0-2 ዲ.ሪ. ኮንጎ
ናሚቢያ 1-3 ቡሩንዲ
ሩዋንዳ 5-0 ሞሪሺየስ
ላይቤሪያ 5-0 ጅቡቲ
ቶጎ 0-0 ቱኒዚያ
ጋምቢያ 0-0 ሞሪታንያ
ደቡብ አፍሪካ 0-0 ካሜሮን