ፋሲል ተካልኝ የመከላከያ አሠልጣኝ ሆነ

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው መከላከያ የቀድሞ ተጫዋቹን በአሠልጣኝነት ሾመ።

ለቀጣይ ዓመት ቡድኑን እያዋቀረ የሚገኘው መከላከያ ከደቂቃዎች በፊት ፋሲል ተካልኝን ዋና አሠልጣኝ አድርጓል። ከቀናት በፊት ዮሐንስ ሳህሌን እንደማያስቀጥል ይፋ አድርጎ የነበረው ቡድኑ ከቀድሞ ተጫዋቹ ጋር ድርድር ሲያድድግ ቆይቶ በመጨረሻም ስምምነት ፈፅሟል።

በ1990’ዎቹ መጨረሻ በተጫዋችነት በመከላከያ ቤት ግልጋሎት የሰጠው ፋሲል በዘንድሮ የውድድር ዓመት በአዳማ ከተማ አሳልፎ የነበረ ሲሆን በመጨረሻዎቹ ስድስት ሳምንታት ግን ከክለቡ ጋር ተለያይቶ ነበር። አሁን ደግሞ በአንድ ዓመት ውል ጦሩን ለማሰልጠን ፊርማውን አኑሯል።

በተያያዘ ዜና መከላከያ የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ በለጠ ወዳጆን ውል ማራዘሙም ታውቋል።