የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየቀረበ ነው

ሀዋሳ ላይ እየተደረገ በሚገኘው ሻምፒዮና የፊታችን ዕሁድ ለሚደረጉ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች የደረሱ ቡድኖች ተለይተዋል።

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አዘጋጅነት በሀዋሳ ከተማ በአርባ ሁለት ቡድኖች መካከል ሲደረግ ቆይቶ በመጨረሻም ወደ አስራ ስድስት ውስጥ እና ወደ አንደኛ ሊግ አስራ ስድስቱንም ያስገባው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተካሄዱ ጨዋታዎች ወደ ሩብ ፍፃሜ የገቡ ስምንት ክለቦች የተለዩበት ውጤት ተመዝግቦበታል፡፡

ዛሬ የተካሄዱ ጨዋታዎች የተመዘገቡ ውጤቶች

ሆሞሻ ሸንጋ 2-4 አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ

ኦሮሚያ ፖሊስ 0-0 ቅበት ከተማ

ኦሮሚያ ፖሊስ 4-5 ቅበት ከተማ (በመለያ ምት)

በደሌ ከተማ 3-0 ቤተል ድሪመር

ሀላባ ሸገር 1-3 አለታ ወንዶ ከተማ

ሻኪሶ ከተማ 5-1 ዶሬ ባፋኖ

አዴት ከተማ 1-1 ሞጣ ከተማ

(የመለያ ምት አዴት ከተማ 6-1 ሞጣ ከተማ)

ሀርቡ ከተማ 1-1 ዳባት ከተማ

ሀርቡ ከተማ 9-10 ዳባት ከተማ (በመለያ ምት)

ሁርሙድ 1-4 ሶኮሩ ከተማ

በውጤቱ መሠረት በደሌ ከተማ ፣ አለታ ወንዶ ከተማ ፣ ሻኪሶ ከተማ ፣ አዴት ከተማ ፣ ዳባት ከተማ ፣ ሶኮሩ ከተማ ፣ ቅበት ከተማ እና አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ወደ ሩብ ፍፃሜው መግባታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን የፊታችን ዕሁድ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ላይ ጨዋታቸው ያከናውናሉ፡፡

ዳባት ከተማ  3:00 ሶኮሩ ከተማ

ሻኪሶ ከተማ  5:00  አዴት ከተማ

በደሌ ከተማ  7:00  አለታ ወንዶ

አዲስ አበባ ዩ/ቲ  9:00 ቅበት ከተማ

በአራት ቡድኖች መካከል የተደረገው የሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከቀናቶች በፊት በሞጆ ከተማ አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡