ሄኖክ አየለ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ተቀላቅሏል

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ሄኖክ አየለ በቀጣዩ የውድድር ዓመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ ለማድረግ ፊርማውን አኑሯል፡፡

ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዳግም የመመለስ ዕድልን ያገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስብስቡን ለማጠናከር በዝውውር ገበያው እየተሳተፈ ሲገኝ አሁን ደግሞ ቀድሞ ቅድመ ስምምነት ላይ ደርሶ ከነበረው ሔኖክ አየለ ጋር ውሉን በፊርማ አፅንቷል።

የቀድሞው የደቡብ ፓሊስ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ ዲላ ከተማ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የነበረው ሔኖክ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ከሀዋሳ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አምርቶ ግልጋሎት መስጠቱ የሚታወስ ሲሆን ቀጣይ መዳረሻውን አዲስ አዳጊው ኤሌክትሪክ ማድረጉ ታውቋል።