ለ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት 48 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበላቸው

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አሠልጣኝ የሆኑት እድሉ ደረጄ ከፊታቸው ላለባቸው የሴካፋ ውድድር ለ48 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

ግብፅ በምታስተናግደው የ2023 ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆነውን የሴካፋ ዞን ተወካይ ለመለየት እንደ ማጣሪያ የሚያገለግለው የቀጠናው ውድድር በሱዳን አስተናጋጅነት ከጥቅምት 12 እስከ 23 እንደሚደረግ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በምድብ 2 ከታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ጋር መደልደሉ ከሰዓታት በፊት ይፋ መሆኑ ይታወቃል። በዛሬው ዕለት የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ሆነው የተሾሙት እድሉ ደረጄ እና ረዳቶቻቸው ለውድድሩ ዝግጅት ይረዳ ዘንድ ለ48 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በድረ-ገፁ ይፋ አድርጓል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ከነገ ጀምሮ በመሰባሰብ ዝግጅት እንደሚጀምሩ ተመላክቷል።

ግብ ጠባቂዎች

1 አስቻለው በየነ / ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
2 ዓለማየሁ አበበ / ሲዳማ ቡና
3 አቤኔዘር ፈይሳ / ኢትዮጵያ ቡና
4 አየኸኝ ዋለልኝ / ሀዋሳ ከተማ

ተከላካዮች

1 ይስሃቅ ከነአ / ሲዳማ ቡና
2 ናትናኤል ናሴፎ / ወላይታ ድቻ
3 ኬኔዲ ከበደ / ወላይታ ድቻ
4 ባይ ኩይት / አዲስ አበባ ከተማ
5 ሙስተጃብ በድሩ / ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
6 ፉአድ ኢብራሂም / አዳማ ከተማ
7 ብሩክ ታረቀኝ / ቅዱስ ጊዮርጊስ
8 ገለታ ኃይሉ / ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
9 አብዲ ዋበላ / አዳማ ከተማ
10 ሻሂዱ ሙስጠፋ / ቅዱስ ጊዮርጊስ
11 ኢዮዳስ ዳዊት / መቻል
12 ዳግም ወንድሙ / ሀዋሳ ከተማ
13 በረከት ወርቁ / መከላከያ
14 ቢንያም ጎዳና / ኢትዮጵያ መድን

አማካዮች

1 አብዱልባሲጥ ከማል / ሀዋሳ ከተማ
2 አቡበክር ሸምሱ / አርባምንጭ ከተማ
3 ሳምሶን ቹቹ / ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
4 ኪያር መሐመድ / ቅዱስ ጊዮርጊስ
5 ከማል ሀጂ / አዲስ አበባ ከተማ
6 ፉአድ አብደላ / ቅዱስ ጊዮርጊስ
7 አብይ ሰለሞን / ቅዱስ ጊዮርጊስ
8 ይትባረክ ሰጠኝ / ኢትዮጵያ መድን
9 ወገኔ ገዛኸኝ / ኢትዮጵያ መድን
10 ዳግም ዮሐንስ / ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
11 ቡጣቃ ሻመና / አርባምንጭ ከተማ
12 ኤርሚያስ ሹምበዛ / ኢትዮጵያ ቡና
13 ሄኖክ ገብረህይወት / ኢትዮ ኤሌክትሪክ
14 ብሩክ ያሬድ / ሀዋሳ ከተማ
15 ብሩክ ታደሰ / ሀዋሳ ከተማ
16 ይታገሱ ታሪኩ / ኢትዮጵያ ቡና

አጥቂዎች

1 ዮሴፍ ታረቀኝ / አዳማ ከተማ
2 ዘላለም አባተ / ወላይታ ድቻ
3 ቃልኪዳን ዘላለም / ወላይታ ድቻ
4 ሚሊዮን ኃይሉ / ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
5 ሄኖክ ኤርሚያስ / ኢትዮጵያ መድን
6 አማኑኤል አድማሱ / ኢትዮጵያ ቡና
7 ከድር አሊ / ኢትዮጵያ ቡና
8 ቧይ ጆን / አዲስ አበባ ከተማ
9 አሸብር ደረጄ / ኢትዮጵያ መድን
10 ኢብራሂም መሀመድ / መቻል
11 ሀብቶም ገብረእግዚአብሄር / ቅዱስ ጊዮርጊስ
12 ዮርዳኖስ ፀጋዬ / ሀዋሳ ከተማ
13 ተገኑ ተሾመ / ቅዱስ ጊዮርጊስ
14 ፍፁም አብርሃም / ሲዳማ ቡና