ከፍተኛ ሊግ | ቡታጅራ ከተማ አስራ አራት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆነው ቡታጅራ ከተማ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈፅም የነባሮችን ውልም አራዝሟል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ ላይ ተሳታፊ ከሆኑ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ቡታጅራ ከተማ ከቀናቶች በፊት አሰልጣኝ ያለው ተመስገንን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ ቡድኑን የሚያገለግሉ አስራ አራት አዳዲስ ተጫዋቾች በይፋ አስፈርሟል።

የቀድሞው የወላይታ ድቻ እና ጅማ አባጅፋር ተከላካይ ውብሸት አለማየሁን ጨምሮ ምንተስኖት የግሌ ግብ ጠባቂ ከድሬዳዋ ፣ ዮናስ ወልዴ አማካይ ከደቡብ ፓሊስ ፣ ልዑል ኃይሉ አጥቂ ከደቡብ ፓሊስ አቤኔዘር ቾንቤ ተከላካይ ከደቡብ ፓሊስ ፣ መሀመድ ናስር አጥቂ ከወልቂጤ ከተማ ፣ ክንዴ አብቹ አጥቂ ከጌዲኦ ዲላ ፣ መሀመድ ሁሴን አማካይ ከየካ ፣ ሔኖክ መርሹ ተከላካይ ከሀረር ሲቲ ፣ ካሣሁን ገብረሚካኤል አማካይ ከየካ ፣ ኤርሚያስ ሰብሬ ተከላካይ ከአርባምንጭ ፣ ምንተስኖት ዮሴፍ አማካይ ከወልቂጤ ፣ ብሩክ ዋቆ ተከላካይ ከአርባምንጭ እና መስፍን ፀጋዬ ግብ ጠባቂ ከመቂ አስፈርሟል።

ቡታጅራ ከላይ ከተዘረዘሩት አዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪም አስራ አንድ በክለቡ የነበሩ ተጫዋቾች ውልም አድሷል።