ኢትዮጵያ ፊፋ የሃገራት ወርሃዊ ደረጃ 123ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች

የአለማቀፉ የእግርኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ በየወሩ በሚያወጣው የፊፋ ኮካ ኮላ የሃገራት ደረጃ ኢትዮጵያ 123ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ በማርች ወር 120ኛ የነበረችው ኢትዮጵያ ከባለፈው ወር ሶስት ደረጃዎችን ወርዳ 123ኛ ሆናናለች፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ በአልጄሪያ ብሊዳ ላይ የ7-1 ሽንፈትን እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ የ3-3 አቻ ውጤትን ኢትዮጵያ በመጋቢት ወር ያስመዘገበችው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሃገራት መካከል 38ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

አልጄሪያ የአፍሪካ መሪነትን ከኬፕ ቬርድ ስትቀበል ግብፅ ጥሩ መሻሻል ያሳየች ሃገር ሆናለች፡፡ ያለፈው ወር በሰንጠረዡ አናት የነበረችው ኬፕ ቬርድ በሞሮኮ በታከታታይ በደረሰባት ሽንፈት ምክንያት ወደ ስድስተኛ ተንሸራታለች፡፡

ባለፈው ወር ከፍተኛ መሻሻል አሳይታ የነበረችው ዩጋንዳ ከዓለም 73ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ የቻን አዘጋጅ የነበረችው ሩዋንዳ 88ኛ ሆናለች፡፡

የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅዋ ጋቦን 89ኛ እንዲሁም በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ራሷን ከአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ውጪ ያደረገችው ቻድ 98ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

ምስራቅ አፍሪካዊያኑ ሶማልያ፣ ኤርትራ እና ጅቡቲ ደግሞ የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡ ሃገራቱ የሚበልጡት ቶንጋን ብቻ ሲሆን ኤርትራ እና ሶማልያ በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ተሳታፊ አይደሉም፡፡ ቻድ እና ጊኒ ቢሳው አስገራሚ በሚባል መልኩ ከፍተኛ የደረጃ መሻሻል ያሳዩ ሃገራት ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *