የ2016 ኦሬንጅ ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡ አላፊ ቡድኖች ቀጥታ ወደ ምድብ ማጣሪያ ስለሚገቡ በጨዋታዎች መካከል ከፍተኛ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ እና የሱዳኑ ኤል-ሜሪክ በውድድሩ ላይ ምስራቅ አፍሪካን የሚወክሉ ብቸኛ ቡድኖች ሲሆኑ የሰሜን አፍሪካ ክለቦች አሁንም በሃያልነታቸው ለመቀጠል በቻምፒየንስ ሊጉ ይፋለማሉ፡፡
ያንግ አፍሪካ ከሰሜን አፍሪካ ቡድኖች ጋር ያለውን መጥፎ ሪከርድ ለማሻሻል የግብፁን አል አሃሊ ዳሬ ሰላም ላይ ይገጥማል፡፡ ያንጋ በንፅፅር የቀለሉ ተጋጣሚዎች በቅድመ ማጣሪያው እና በመጀመሪያው ዙር የገጠመ ሲሆን አሁን ወደ ምድብ ለመግባት አንድ መሰናክል ብቻ ተደቅኖበታል፡፡ የታንዛኒው ስኬታማ ክለብ ያንግ አሰልጣኝ የሆኑት የቀድሞዎ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ትውልደ ሆላንድ ጋናዊው ሃንስ ቫን ደር ፕልዩም ብድናቸው የ2014ቱን ስህተት ላለመድገም እንሚጫወቱ ተዘግቧል፡፡ ያም ሆኖ አል አሃሊ የታንዛኒያ ክለቦችን ለማሸነፍ ሲቸገር አይስተዋልም፡፡
ኤል-ሜሪክ የ2014 ካፍ ቻምፒየንስ ሊጉ አሸናፊው የአልጄሪያው ኢኤስ ሴቲፍን ኦምዱሩማን ላይ ያስተናግዳል፡፡ ሜሪክ እና ሴቲፍ በ2015 ቻምፒየንስ ሊግ በምድብ ሁለት አንድ ላይ ተደልድለው የነበረ ሲሆን ሜሪክ እስከ ፍፃሜ ግማሽ ድረስ መጓዘ ችሏል፡፡
የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ የዓምና አሸናፊው ቲፒ ማዜምቤን ይገጥማል፡፡ ከአምናው የቻምፒየንስ ሊግ ጉዞው በጣም የወረደ አጨዋወትን ይዞ የውድድር ዘመኑን የጀመረው የሉቡምባሺው ክለብ በሞሮኮው ሻምፒዮን ይፈተናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዛማሌክ በሰሜን አፍሪካ ደርቢ ኤምኦ ቤጃን ይገጥማል፡፡ ቤጃ በአንደኛው ዙር ባልተጠበቀ መልኩ ክለብ አፍሪካን ከውድድር አስወጥቷል፡፡
የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች
ቅዳሜ
15፡30 – አሴክ ሚሞሳ (ኮትዲቯር) ከ አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) (ስታደ ሮበርት ቻምፕሮ)
16፡00 – ያንግ አፍሪካ (ታንዛኒያ) ከ አል አሃሊ (ግብፅ) (ቤንጃሚን ማክፓ ናሽናል ስታዲየም)
18፡00 – ስታደ ማሊያን (ማሊ) ከ ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) (ስታደ ኦምኒስፖርትስ ማዲቦ ኬታ)
19፡30 – ዋይዳድ ካዛብላንካ (ሞሮኮ) ከ ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) (ግራንድ ስታደ ማራካሽ)
20፡00 – ዛማሌክ (ግብፅ) ከ መውሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃ (አልጄሪያ) (ፕትሮ ስፖርት ስታዲየም)
20፡00 – ኤል-ሜሪክ (ሱዳን) ከ ኢኤስ ሴቲፍ (አልጄሪያ) (ኤል-ሜሪክ ስታዲየም)
ዕሁድ
15፡30 – ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ.ኮንጎ) ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ስታደ ታታ ራፋኤል)
16፡00 – ኢኒምባ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ) ከ ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ (አዶኪ አሚሰማካ ስታዲየም)