አዞዎቹ ተከላካይ አስፈርመዋል

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት የተለያየው ተከላካይ አሳዳጊ ክለቡን ዳግም ተቀላቅሏል።

\"\"

በአሠልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመራው አርባምንጭ ከተማ 13 ነጥቦችን በማግኘት በሰበሰበው ቁጥር ልክ 13ኛ ደረጃን በፕሪምየር ሊጉ ይዞ መቀመጡ ይታወቃል። የሚታወቅበትን ጠጣር የመከላከል አደረጃጀት ዘንድሮ ለማስመልከት እየተቸገረ የሚገኘው ቡድኑ በአራት እና አምስት የተከላካይ ክፍል መዋቅር ሲጫወት የሰነበተ ሲሆን አሁን ደግሞ በተከላካይ ክፍሉ ላይ አዲስ ተጫዋች ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል። ክለቡን የተቀላቀለው ተጫዋች አበበ ጥላሁን ነው።

\"\"

አበበ ከአርባምንጭ ከተማ የታዳጊ ቡድን ተነስቶ ዋናውን ቡድን በማገልገል ወደ ሲዳማ ቡና፣ መከላከያ (መቻል) እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና አምርቶ መጫወት የቻለ ሲሆን የስድስት ወር ቀሪ ኮንትራት እየቀረው ከቡናማዎቹ ጋር በስምምነት መለያየቱ ይታወቃል። ተጫዋቹም ወደ አሳዳጊ ክለቡ በማምራት የአንድ ዓመት ተኩል ፊርማውን ማኖሩ ተገልጿል።