በአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊ ዳኛ ግልጋሎት ይሰጣሉ

ዛሬ በሚጀምረው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊው ረዳት ዳኛ ተሳትፎ ያደርጋሉ።

\"\"

ከ2022 ወደ 2023 የተሸጋሸገው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ከየከቲት 12 እስከ መጋቢት 2 ድረስ በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ግብፅ ይደረጋል። ውድድሩ በዛሬው ዕለት ከመጀመሩ በፊት የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ አካል የሆነው ካፍ በአንፃራዊነት ወጣት ያላቸውን የአህጉሪቱ ዳኞች መምረጡ ታውቋል።

በዚህም በውድድሩ ላይ ካፍ ከ30 የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት 16 ዋና፣ 18 ረዳት እንዲሁም 6 የቪ ኤ አር ዳኞችን የመረጠ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ፋሲካ የኋላሸት መመረጡ ታውቋል።

\"\"