ከፍተኛ ሊግ | ንብ ዘጠኝ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

አስራ አራት ተጫዋቾችን ያሰናበተው ንብ በተቃራኒው ዘጠኝ አዳዲሶችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ በአሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ መሪነት የመጀመሪያውን ዙር ከመሪው አዲስ አበባ ከተማ በሰባት ነጥቦች አንሶ ስምንኛ ላይ ተቀምጦ ዙሩን ያገባደደው ንብ ክለብ በሁለተኛው ዙር በይበልጥ ተጠናክሮ ለመቅረብ በማሰብ ሦስት ግብ ጠባቂዎችን ጨምሮ በድምሩ አስራ አራት ተጫዋቾችን በይፋ ሲያሰናብት ዘጠኝ አዳዲሶችን በአንፃሩ ደግሞ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

\"\"

ታሪክ ጌትነት ዳግም ወደ እግር ኳስ ተመልሷል። በአዳማ ከተማ እያለ ከአንድ ዓመት በፊት በገጠመው ጉዳት ከእግር ኳሱ ርቆ የቆየው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ፣ ደደቢት እና ሀድያ ሆሳዕና ግብ ጠባቂ ንብን እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ተቀላቅሏል።


በዲላ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ እና በያዝነው ዓመት አገማሹን በለገጣፎ የለገዳዲ የቆየው አጥቂው አላዛር ዘውዴ ፣ በወልቂጤ ከተማ እና እንጅባራ የተጫወተው ተከላካዩ ይበልጣል ሽባባው ፣ ከዚህ ቀደም ለክለቡ ተጫውቶ ያሳለፈው ተከላካዩ አንተነህ መሰለ ፣ ወላይታ ድቻ እና ነቀምት ከተማ የተጫወተው የመስመር አጥቂው ታምራት ስላስን ጨምሮ ሳሙኤል ጀሀድ ግብ ጠባቂ ከመድን ተስፋ ፣ ጆንቴ ገመቹ ከሱሉልታ ፣ ምስክር መለሰ የመስመር አጥቂ ከቦዲቲ እና ወንድማገኝ አበራ ከአረካ ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራሚዎች ሆነዋል።

\"\"