ከፍተኛ ሊግ | ሻሸመኔ ከተማ በአዳዲስ ተጫዋቾች ስብስቡን አጠናክሯል

በምድብ ለ በግብ ክፍያ ብቻ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ሻሸመኔ ከተማ የሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል።

\"\"

የካቲት 1 ተከፍቶ በነበረው የከፍተኛ ሊግ የዝውውር መስኮት በርካታ ክለቦች ቡድናቸውን ሲያጠናክሩ ቆይተዋል። ከእነኚህም ክለቦች መካከል ከአዲስአበባ ከተማ ጋር በነጥብ ዕኩል (24) በግብ ክፍያ አንሶ ሁለተኛ ላይ የተቀመጠው ሻሸመኔ ከተማ በአሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ መሪነት ሁለተኛው ዙር ለመጠናከር ሦስት ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል።

\"\"

ፉዐድ መሐመድ የመስመር አጥቂ ከየካ ፣ ሮብሰን በዳኔ አማካይ ከአርሲ ነገሌ እና አብዱልከሪም ቃሲም አጥቂ ከቂርቆስ ክፍለከተማ ቡድኑን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራማዎች ሲሆኑ የጌታለም ማሙዬን ውልም ክለቡ ማደሱን አሳውቆናል።