አሠልጣኝ ውበቱ አዲስ ተጫዋች ጠርተዋል

በትናንትናው ዕለት በጉዳት ከዋልያዎቹ ስብብስብ ውጪ በሆነው አጥቂ ምትክ አሠልጣኝ ውበቱ አንድ የመስመር አጥቂ ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

\"\"

በሦስት ቀናት ልዩነት ከጊኒ ጋር ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ዝግጅቱን እያከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኋላ ከሩዋንዳ ጋር የአቋም መፈተሻ ያደርጋል። በዝግጅት ወቅት የስብስቡ አካል የነበረው አጥቂው ይገዙ ቦጋለ ጉዳት አስተናግዶ ከስብስቡ ውጪ እንደሆነ ዘግበን የነበረ ሲሆን በምትኩ ሌላ ተጫዋች መጠራቱ ይፋ ሆኗል።

በዚህም የቅዱስ ጊዮርጊሱ የመስመር አጥቂ ቸርነት ጉግሳ አዲስ ጥሪ የተደረገለት ተጫዋች ነው። ተጫዋቹ ዛሬ ረፋድ ስብስቡን የተቀላቀለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም ለሩዋንዳ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርገው ስብስብ ጋር አዳማ ይገኛል።

\"\"