የዋልያዎቹ ተጋጣሚ አንድ ተጫዋቿ ተጎድቶባታል

ከቀናት በኋላ ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች ከኢትዮጵያ ጋር ያለባት ጊኒ አንድ ተጫዋቿ ተጎድቶባት በምትኩ ለሌላ ተጫዋች ጥሪ አስተላልፋለች።

አይቮሪኮስት ለምታስተናግደው የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ አራት ከግብፅ፣ ጊኒ እና ማላዊ ጋር ተደልድሎ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን መጋቢት 15 እና 18 ደግሞ ሞሮኮ ላይ ከጊኒ ጋር የምድብ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታውን ለማከናወን እየተሰናዳ ይገኛል።

\"\"

ተጋጣሚያችን ጊኒም ከቀናት በፊት ለጨዋታዎቹ 23 ተጫዋቾችን ጠርታ የነበረ ቢሆንም የፈረንሳዩ ስታድ ሬም ንብረት የሆነው እና በውሰት ለቤልጂየሙ ዩፐን የሚጫወተው የ19 ዓመቱ ተከላካይ ኢብራሂም ዲያኪቲ በጉዳት ከስብስቡ ውጪ መሆኑ ተመላክቷል። የቡድኑ አሠልጣኝ ካባ ዲያዋራም በወጣቱ ተጫዋች ምትክ በቡልጋሪያ ሊግ ለሚጫወተው የግራ መስመር ተከላካይ ፓ ሞሞዱ ኮናቴ ጥሪ አስተላልፈዋል።

\"\"

ሞሞዱ ከዚህ ቀደም ስምንት ጨዋታዎችን ለብሔራዊ ቡድኑ ያደረገ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ በክለቡ 16 ጨዋታዎችን አከናውኖ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።